ታላቁ የህዳሴ ግድብ

18 June 2013
ታላቁ የህዳሴ ግድብ

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ በአሶሳ በኩል 877 ኪሎ ሜትር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልል መንግስት ውስጥ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለ ሲሆን፣የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ 6000 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት...

You are here: Home

አባይ ለመጀመሪያ ጊዜ አቅጣጫውን በመቀየር ሊፈስ ነው፡፡

Rate this item
(0 votes)
22
Jul
2013

የታላቁ አባይ ወንዝ ማክሰኞ ግንቦት 20/ቀን 2005 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አቅጣጫውን ቀይሮ ሊፈስ መሆኑን ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክርቤት በተገኘው መረጃ ተገለፀ፡፡ የአባይ ወንዝ ለመጀመሪያ ጊዜ አቅጣጫውን የሚቀይርበትን ቀን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት እንደገለፀው ወንዙ አቅጣጫውን የማስቀየር ደረጃ ላይ መደረሱ ግድቡ ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩንና ስራው በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ያሳያል፡፡ ግድቡ አቅጣጫውን የሚቀይርበት ቀን ከግንቦት 20 ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አስከፊውን የደርግ ስርዓት ከገረሰሱበት የድል ቀን ጋር መገጣጠሙ በራሱ ልዩ ያደርገዋል፡፡ በግድቡ ግንባታ ምክንያት ወንዙ አቅጣጫውን ቀይሮ መፍሰስ በመጀመሩ ለዘመናት ሳይደፈር በቆየው አባይ ላይ የመጀመሪያውን ድል መቀዳጀታችን የሚያሳይ ከመሆኑ ባሻገር ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ የደስታ ስሜት የሚያጭር ነው በማለት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ያስተላለፈው ፅ/ቤቱ በግድቡ ግንባታ ላይ የተጀመሩት የሃብት ማሰባሰብ ስራዎች ተጠናክረው በመቀጠል ግድቡ በታቀደው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባው ገልጠዋል፡፡ በቅርቡ በክቡር ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራር ቡድን ቦታው ድረስ ተገኝቶ በተመለከተው የግድቡ ስራ ሂደት መርካቱንና ስራው በተጀመረበት ፍጥነት እንዲቀጥል የአደራ ቃል ማስተላለፉን እንዲሁም ለዚሁ የሚያስፈልግ ሃብት ለማሰባሰብም የከተማዋውን ህዝብ ወክሎ ቃል መግባቱን ያስታወሰው ፅ/ቤቱ ፣ነዋሪው ከዚህ በፊት እንደጀመረው የሃብት ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ እንዲረባረብ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Web-Administrator

የአዲስ አበባ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ቲም

Website: www.aagerd.gov.et

ማኅበራዊ ድህረገፆች

ስለ ፅ/ቤቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 41/2003 ተቋቁሟል፡፡

ምክርቤቱ በደንቡ አንቀፅ ፺ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባራት በአግባቡ ስራ ላይ ለማዋልና የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት እንዲችል በደንቡ አንቀፅ 8 ላይ የምክር ቤቱ ፅ/ቤት እንደሚቋቋም ተደርጓል ፡፡